Discover
DW | Amharic - News

3275 Episodes
Reverse
የማህበራዊ መገናኛ መድረኩ በእርግጥ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች የፈጠራ አቅማቸውንና ተሰጥኦዋቸውን እንዲያሳዩ፣ ከእኩዮቻቸው ጋር ትስስር እንዲፈጥሩና አዳዲስ የገቢ ማግኛ ሥልቶችን እንዲቀይሱ የዕድል በር መክፈቱ አይታበልም፡፡ ጥቂት የማይባሉ እዚህ ግባ ከማይባል ቦታ ተነስተው በአጭር ጊዜ ውስጥ ዝና አትርፎላቸዋል።
በአውስትራሊያ ሲድኒ ከተማ ቦንዲ በተባለው የባሕር ዳርቻ የይሁዲዎች ሐኑካ ሲከበር ሁለት ግለሰቦች በከፈቱት ተኩስ 12 ሰዎች ሲገደሉ 29 ሰዎች ቆሰሉ። ከጥቃት ፈጻሚዎቹ አንዱ በፖሊስ ሲገል ሌላው ቆስሎ በቁጥጥር ሥር ውሏል።
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ አፍሪቃን የተመለከተው አዲሱ መርህ ምን ይዞ ነው የመጣው የሚለው ማነጋገር ጀምሯል። አዲሱ የትራምፕ የአፍሪቃ መርህ ከእርዳታ ይልቅ ንግድ በተለይም ጥሬ ሀብቶች ላይ ያተኮረ ነው።
ቤኒን ውስጥ የመጨረሻው መፈንቅለ መንግሥት የተካሄደው በጎርጎሪዮሳዊው 1972 ነበር። በዚህም ምክንያት ላለፉት ጥቂት የማይባሉ አስርት ዓመታት ምዕራብ አፍሪቃዊቱ ሀገር ዴሞክራሲያዊ አስተዳደሯ እያደገ በመሄድ ላይ ነው የምትባል ሞዴል ሆና ቆይታለች።
ኢጋድ ኤርትራ ለቀጣናው ሰላም፣ መረጋጋት እና ልማት የጋራ ግቦችን ለማራመድ አቋሟን እንደገና እንድታጤን እና ሙሉ በሙሉ ወደ ድርጅቱ አባልነት እንድትመለስ እንደሚያበረታታ አስታውቋል።
ኤርትራ ከኢጋድ አባልነት ራሷን ለማግለል መወሰኗ እንዳሳዘናት የወቅቱ ሊቀ-መንበር ጅቡቲ ገለጸች። ኤርትራ ለሁለተኛ ጊዜ ጥላ ስትወጣ ኢጋድ “ለቀጠናው መረጋጋት ጉልህ አስተዋጽዖ ማበርከት” እንደተሳነው ተችታለች። ኤርትራ ክፍለ አኅጉራዊውን ድርጅት ከተቀላቀለችም በኋላ “በስብሰባዎች፣ ፕሮግራሞች ወይም እንቅስቃሴዎች” አለመሳተፏን ኢጋድ አስታውቋል።
ኢትዮጵያ እና ኤርትራ “ማንኛውንም ውጥረት ወይም አለመግባባት በሰላማዊ እና በዲፕሎማሲያዊ መንገድ እንዲፈቱ” የአውሮፓ ኅብረት እና ብሪታኒያን ጨምሮ ሀገራት ጥሪ አቀረቡ። ሀገራቱ የአልጀርስ ሥምምነትን 25ኛ ዓመት እያስታከኩ ያወጧቸው መግለጫዎች በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል ያለው ውጥረት እንዳሳሰባቸው የሚጠቁሙ ናቸው።
የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ በማኅበራዊ መገናኛ አውታሮች ላይ ከማኅበረሰቡ ባህልና ወግ ያፈነገጡ ተግበራትን ፈጽመዋል ብሎ የጠረጠራቸውን በስፋት በቁጥጥር ስር እያዋለ እንደሚገኝ እያሳወቀ ነው።
ጾታን መሰረት ያደረገ ጥቃት በኢትዮጵያ ስር የሰደደ ችግር ቢሆንም፣ በአገሪቱ እየተከሰቱ ባሉ የትጥቅ ግጭቶች ሳቢያ ጥቃቱ እየተባባሰ መምጣቱ ይነገራል። በአማራ ክልል ላለፉት ሁለት አመታት በፌደራል መንግስትና በፋኖ ሃይሎች መካከል እየተካሄደ ያለው ግጭትም በሴቶች ላይ የሚደርሰውን ወሲባዊ ጥቃት ማባባሱን የቅርብ ጊዜ ዘገባዎች ያመለክታሉ።
ብዙ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ግን ኢትዮጵያ ዉስጥ የቀጠሉት ግጭቶች፣ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች፣ የፖለቲካ አለመረጋጋትና ሥርዓተ አልበኝነት ሳይወገዱ ወይም ሳይቃላሉ ምርጫ ማድረግ ያስቸግራል እያሉ ነዉ
ውይይት፦ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚከሰተው ግጭት ሱዳን ውስጥ፥ የሱዳኑ ኢትዮጵያ ውስጥ ነጸብራቁ በጉልኅ ይታያል ። ከፍ ሲል ግብጽ ከወደታች ደግሞ ሶማሊያም በግጭት ውጥረቱ ስማቸው በተደጋጋሚ ይነሳል ። የኢትዮጵያ መንግሥትን ደግፎ በትግራይ ክልል ጦር ያዘመተው የኤርትራ መንግሥት ያኔ ከደገፈው ጋር አሁን ዐይን እና ናጫ ከመሆንም አልፈው ተፋጥጠዋል ።
በአሁኑ ጊዜ እንደ ቲክ ቶክ ያሉ የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች የሰዎችን ሀሳብ በመበታተን ይጠቀሳሉ።በዚህ የተነሳ በርካታ ሰዎች ከጥቂት ደቂቃዎች በላይ በአንድ ነገር ላይ ማተኮር እየተቸገሩ መሆኑን ጥናቶች ያሳያሉ።ይህ እንዴት ይከሰታል? እንደ ቲክ ቶክ ያሉ የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች በአእምሯችን ላይ ምን ተፅዕኖስ ያሳድራሉ?
የመተግበሪያ አጠቃቀምን በተመለከተ በተለያዩ ድረ ገፆች የወጡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት በ2024 ዓ/ም ተጠቃሚዎች አውርደው የተጠቀሙባቸው መተግበሪያዎች የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ናቸው። በቻይናው ኩባንያ ባትዳንስ የተሰራው እና በአሜሪካ የመዘጋት አደጋ የተጋረጠበት ቲክቶክ /TikTok/ በ2024 በብዛት የተጫነ መተግበሪያ ሆኗል።
ሌላው አስተያየት ሰጪ ተሽከርካሪውን ከባንክ ብድር ወስዶ መግዛቱን ጠቅሶ በቤንዚን እጥረቱ ምክንያት ሰርቶ ብድር መመለስ እንዳልቻለ ገልጧል፣ አንዴ ነዳጅ ከቀዳ ሌላ ጊዜ ለመቅዳት ሳምንት እንደሚጥብቅ አመልክቷል፣ ያን ላለማድረግ ደግሞ በውድ ዋጋ ከህገወጥ ነጋዲዎች ቤንዚን ገዝቶ እንደሚሰራ ነው ያስረዳው።
የትናንትናውን ጨምሮ ባለፉት ሳምንታት ውስጥ አዲስ አበባ ድረስ ዘልቆ በተሰማው የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት ሳቢያ ከእልቅልፋችን እየቀሰቀሰን ሰላም አሳጥቶናል በማለት የሚያማርሩ የህብረተሰብ አካላት ቁጥርም ቀላል አይደለም፡፡
ተመራጭ ፕሬዝዳንት ትራም እራሳቸውም ሰኞ እለት ለአንድ ሜዲያ በሰጡት አስተያየት ፕሬዝዳንት ፑቲንም ከሳቸው ጋር መገናኛኘቱን እንደሚፈለጉትና ከሰኞው በዓለ ሹመት በሗላ እንደሚገናኙ ያላቸው እመነት በመግለጽ ይህ ሁለቱንም በተለይም ዩክሬንን እያወድመ ያለ ጦርነት ባስችኳይ መቆም እንድላበት እንደሚያምኑ አስታውቀዋል።
የውጭ ዜጎች እድሉን ካገኙና ከተጣጣሩ በጀርመን ስኬታማ መሆን መቻላቸው ማሳያ የሆኑት አቶ ሳምሶን በአሁኑ ጊዜ ስደተኞች በምርጫ ዘመቻ ወቅት ስማቸው መጉደፉና ስብእናቸውም ዝቅ ተድርጎ መቅረቡ በጣም ይሰማቸዋል።ስደተኛን የሚጠሉት ቀኝ አክራሪዎች ጀርመን ውስጥ እየተጠናከሩ መምጣታቸው ከሚያሳስባቸው አንዱ ኤሌክትሪካል ኢንጅነር ሳምሶን በቀለ ናቸው።
50 በአፍሪቃ እና አውሮጳ የሚንቀሳቀሱ አኅጉራዊ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች የኢትዮጵያ መንግሥት ጠንካራ ሲሺክ ድርጅቶች ላይ የሚወስደውን ያልተገባ ያሉትን ርምጃ እንዲያቆም ጠየቁ ። ድርጅቶቹ የኢትዮጵያ መንግሥት በሲቪክ እና የመገናኛ ብዙኃን ዘርፎች ላይ እያደረገ ያለውን ተጽእኖ እንዲያቆም ግፊት እንዲያደርጉ ጥሪ አስተላልፈዋል ።
በአሜሪካዋ ሎስ አንጀለስ ግዛት ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ ዕለት የተነሳው የሰደድ እሳት እስካሁን በቁጥጥር ስር እንዳልዋለ እየተነገረ ነው። በዚህ ጊዜ ውስጥም እሳቱ ከ20 ሺህ ሄክታር በላይ አካባቢን ያዳረሰ ሲሆን እሳቱን ለማጥፋት ከ1,400 በላይ የእሳት አደጋ ተከላካይ ሠራተኞች ተሠማርተዋል። ሰደድ እሳቱን ያስነሳው ምክንያት እየተመረመረ ነው።
ተፈናቃዮች ወደቀዬአቸው እንዲመለሱ የፌደራል መንግስቱ ሕጋዊ እና ሞራላዊ ኃላፊነቱን ይወጣ ሲል የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ጥሪ አቀረበ ። ከዚህ በተጨማሪ ጊዜያዊ አስተዳደሩ ባሰራጨው መግለጫ የአፍሪቃ ኅብረት፣ የአሜሪካ መንግስት እና የአውሮፓ ኅብረት የፕሪቶርያው ውል እንዲፈፀም ጫና ይፍጠሩ ብሏል።






















